እንክዋን ደህና መጡ

EOTC SChool

የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የኦንላይን ትምህርት ማእከል

EOTC SCHOOL

ዛሬ ነገ ሳይሉ
ይመዝገቡ

የሥልጠናው ሂደት

ይህ የመማሪያ ድረ ገጽ በየትኛውም ዓለም የሚኖር ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ገብቶ እንዲማርበት የተዘጋጀ ሲኾን ይኸውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ ቀኖና እንዲሁም ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ መሠረት የተዘጋጀ የመማሪያ ድረ ገጽ ነው፤ ተማሪዎች በያሉበት እንደየዘንባሌያቸው ዕውቀትን እንዲቀስሙ እንደ አእምሯቸው ስፋትና እንደ ዕድሜያቸው ሁኔታ ተመጥኖ ተወስኖ የሚቀርብበት በየዘርፉ ጠቅላላ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀቶች የሚሰጥበት ድረ ገጽ ነው፤ የትምህርቱም አሰጣጥ ቀልጣፋ ጊዜ ቆጣቢ ዘመኑን የሚዋጅ ሥርዓተ ትምህርትን የተከተለ ነው።

ተማሪዎች ከተቋማችን የሚያገኙት ጥቅም

1. እንደ አስፈላጊነቱ ተለዋዋጭና ምቹ በኾነ ሰዓት ተማሪዎች በራሳቸው የአእምሮ ፍጥነት፣ በራሳቸው የጊዜ ሰሌዳ እና ከማንኛውም ቦታ ላይ ኾነው እንዲማሩ የሚያድረግ ፕሮግራም ነው። 2. የትምህርት ሥልጠና በተለይም በሥራ፣ በቤተሰብ ወይም በሌላ ምክንያት የመማር ዕድሉን ማግኘት ላልቻሉ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ ነው። 3. ተቋማችን በአገልግሎቱ ፈጣን በመኾኑ በተቋማችን የሚሰጡ ኮርሶች ለዓለም አቀፍ ታዳሚዎች ተደራሽ ናቸው፣ ጂኦግራፊያዊ እንቅፋቶችን ያስወግዳሉ። የኢንተርኔት አክሰስ ያለው ማንኛውም ሰው ጥራት ያለው ትምህርትን ማግኘት ይችላል።

መምህራን ከተቋማችን የሚያገኙት ጥቅም

1. በኦንላይን ማስተማር ከተለዋዋጭ ሰዓቶች እና ከየትኛውም ቦታ የመሥራት ችሎታን ለማዳበር በር ይከፍትላቸዋል። 2. መምህራን ጊዜን ጉልበትን ገንዘብን ቆጥበው ባሉበት ኾነው ልምዳቸውን በማካፈል ከፍተኛ አድናቆትና አክብሮት የሚያገኙበት ፕሮግራም ነው፤ 3. መምህራን የራሳቸውን መርሐ ግብሮችን ቀርፀው ከቤታቸው ሆነው ማስተማር ስለሚችሉ ይህ ልምድ ወደ ተሻለ የሥራ ሕይወት ሚዛን ያመራቸዋል።

ተማሪዎች ስለ ሶሻል ሚዲያችን ምን ይላሉ

የራሱ የሆነ
ሶሻል ሚዲያ ያለው

አዳዲስ ኮርሶች ሲወጡ መልዕክት ይድረስዎ

ኢሜሎትን እዚህ ያስቀምጡ

© The Adventurers 2025